ኤርሚያስ አመልጋ ይናገራሉ! “ኃላፊነቴን እወጣለሁ የጀመርኩትን ሥራም እጨርሳለሁ”

በኤርሚያስ አመልጋ
‹‹ታሪክ ራሱን ይደግማል›› ነውና ከዓመታት በፊት በእኔ ላይ የታወጀው የስም ማጥፋት ዘመቻ ይኼው በዚህ ሰሞንም ጊዜ ጠብቆ ዳግም እየተጧጧፈብኝ ይገኛል፡፡

ለሀሜትና ለአሉባልታ ጆሮ የምሰጥ ሰው ባልሆንም፣ ከመሥራት ይልቅ ማውራት የሚቀናቸው አሉባልተኞች በየአቅጣጨው የሚረጩት የወሬ ጥላሸት ንፁህ ማንነቴን ሙሉ ለሙሉ የማጠልሸት አቅም እንደማይኖረው ባውቅም፣ የሴረኞች ገመድ ከረጅሙ ጉዞዬ ጠልፎ ሊጥለኝ እንደማይችል ቢገባኝም… ታሪክ ሲደገምብኝ እያየሁ ‹‹ዝም›› ማለትን አልመረጥኩም፡፡

ከሳምንታት በፊት በዚሁ ጋዜጣ ላይ ከአክሰስ ሪል ስቴት ጋር በተያያዘ የተከሰቱ አንዳንድ ችግሮችንና ምላሽ የሚያስፈልጋቸውን ጉዳዮች በተመለከተ በተጨባጭ መረጃ የተሟላ ማብራሪያ መስጠቴ ይታወሳል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከሪል ስቴት ኩባንያው ጋር በተያያዘ መናፈስ ለጀመረው አሉባልታ ተገቢ ምላሽ የሚሰጠውን ይኼን ጽሑፍ ያነበቡ ሰዎች ያለውን ተጨባጭ እውነታ ለመገንዘብ ይችላሉ የሚል ተስፋ አለኝ፡፡

ይኼም ሆኖ ግን በአክሰስ ሪል ስቴትና በተለይ ደግሞ እንደ ግለሰብ በእኔ ላይ የተከፈተው የስም ማጥፋት ዘመቻ፣ ከወሬነት አልፎ በየጋዜጣውና በየሬዲዮው ላይ ተጧጡፎ መቀጠሉን ሰማሁና እንደገና ለሌላ ጽሑፍ ተዘጋጀሁ፡፡ በመጀመሪያ ግን ይኼን መሰሉ በግል ሰብዕናዬ ላይ የሚያነጣጥር ‹‹በሬ ወለደ›› ዓይነት ዘገባ፣ ለእኔ አዲስ አለመሆኑንና ስም ማጥፋትም ታሪክ ሆኖ በእኔ ላይ መደገሙን ለመግለጽ እፈልጋለሁ፡፡ ‹‹በሲአይኤ ወኪልነት የሚጠረጠረው ባለሀብት ‹ሮያል ክራውን› በሚባል የሽንት ቤት ውኃ ሕዝቡን እየፈጀው ነው›› የሚለው ፍፁም ውሸት የሆነ የሐሰት ውንጀላና ስም ማጥፋት በጋዜጣ ላይ ወጥቶ ለኪሳራ ከዳረገኝ ከአሥራ አራት ዓመታት በኋላ፣ እነሆ ከሰሞኑም ውንጀላውና ስም ማጥፋቱ ዳግም መልኩን ቀይሮና የበለጠ ተጠናክሮ ቀጠለብኝ፡፡ ያኔ ‹‹የሲአይኤ›› ወኪል› የተባልኩት እኔ፣ አሁን ደግሞ በ‹‹ዘራፊነት›› ስሜ ተጠራ፡፡ ከውጭ አገር መጥቼ የሕዝቡን ጤና አደጋ ላይ የሚጥል መርዝ በአደባባይ እየሸጥኩ መሆኑን ከሚያትተው ወሬ ከዓመታት በኋላ፣ ከሰሞኑ ደግሞ የሕዝቡን ገንዘብ በአደባባይ ዘርፌ፣ በስውር ወደ ውጭ አገር መኮብለሌን የሚያሳብቀው እጅ እግር የሌለው መሠረተ ቢስ ዘገባ ተጻፈብኝ፡፡ ይህን መሰሉ የጋዜጣ ላይ ውንጀላ ውሎ ሲያድር መሠረተ ቢስነቱ መረጋገጡ እንደማይቀር ስለማውቅ፣ ለአሉባልታው ምላሽ በመስጠት ጊዜዬን አላባክንም፡፡

ይልቁንም የሚዲያን ዘገባ ሁሉ በሙሉ ልብ አምነው የሚቀበሉ ነገሩ ያልገባቸው የዋሆች አይጠፉምና ‹‹ነገርዬው የተለመደ ድራማ ነው›› ልላቸው ነው አመጣጤ፡፡ ሩቅ ሊራመድ አስቦ የተነሳን ሰው ከእግር ከእግሩ ተከታትሎ ጠልፎ የመጣል ተልዕኮ አንግበው የሚንቀሳቀሱ ተንኮለኞች ጋዜጣ ላይ ያጠመዱብኝን ስውር ገመድ በተመለከተ ግንዛቤ ለሌላቸው አንባቢያን ነው የምጽፈው፡፡ ከ20 ዓመታት የአሜሪካ የትምህርትና የሥራ ቆይታ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስና በኢንቨስትመንቱ ዘርፍ ለመሰማራት የወሰንኩት፣ በወቅቱ በአገሪቱ የነበረው ሁኔታ ለሥራ እንጂ ለዝርፊያ ምቹ መሆኑን በመገንዘብ አይደለም፡፡ አመጣጤም ሠርቶ አገር ለማልማት እንጂ ለመዝረፍ አይደለም፡፡ ገንዘብ ያገኘሁትም ሆነ ሀብታም የሆንኩት እዚህ ሳይሆን አሜሪካ ነው፡፡ በዓለማችን ከፍተኛ ተከፋይ የሆኑ የተመረጡ ባለሙያዎች ተቀጥረው በሚሠሩበት በኒውዮርክ ሲቲው ግዙፍ የፋይናንስ ማዕከል፣ በዎል ስትሪት የነበረኝን ትልቅ ሥራና የተደላደለ ሕይወት ገፍቼ፣ ከ17 ዓመታት በፊት ወደ አገሬ የመጣሁት፣ ዕውቀቴንና ገንዘቤን አዋህጄ በኢንቨስትመንቱ መስክ ርቄ ለመጓዝ በማሰብ ነው፡፡

የአሜሪካ ኑሮዬን ትቼ ለመምጣት ስወስን ብዙዎች እንደ እብድ ነው የተመለከቱኝ፡፡ ምክንያቱም ይህ ድርጊት የተንደላቀቀ ኑሮን መግፋትና ራስን ወደ ፈተና ማስገባት ነው፡፡ እንዳሰብኩትም መንግሥት የፈጠረውን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም በአገሪቱ አዳዲስ የሆኑ የኢንቨስትመንት ሥራዎችን ተግባራዊ ለማድረግና ወደ ስኬት ለመሸጋገር ባለፉት 17 ዓመታት የተጓዝኩበት መንገድ እንዲህ ከሰሞኑ መናፈስ እንደጀመረው አሉባልታ የሕዝቡን ጥሪት ዘርፎ በመሰወር የሚጠናቀቅ አይደለም፡፡ ወደ አሜሪካ ተመልሶ የመኖር ዕቅድ ቢኖረኝ ከኢትዮጵያ አምስት ሳንቲም ይዤ መሄድ አያስፈልገኝም፡፡ በመላው ዓለም በሚገኙ ታላላቅ የፋይናንስ ተቋማት በከፍተኛ ክፍያ ተቀጥሮ መሥራትና በቀላሉ ዶላር ማፈስ የሚያስችል ዕውቀትና የሥራ ልምድ ያለኝ ሰው ነኝ፡፡ በኢትዮጵያ ኢንቨስት አድርጌ ከማገኘው ትርፍ በእጅጉ የሚበልጥ ገቢ በሞያዬ አሜሪካም ሆነ ሌላ አገር ተቀጥሬ ብሠራ ማግኘት እችላለሁ፡፡ ለታላላቅ የአሜሪካ ኩባንያዎች በኢንቨስትመንት ባንኪንግ ዘርፍ የማማከር አገልግሎት በመስጠት፣ በሚሊዮን ዶላሮች የሚቆጠር ገቢ ያገኝ የነበረውን የግል ድርጅቴን ዘግቼ ወደ አገሬ የመጣሁት ‹ከአሜሪካ ሥራ ይልቅ፣ የኢትዮጵያ ዝርፊያ አትራፊ ነው› ብዬ አይደለም፡፡ አገሬ መኖር ስለምፈልግ ነው የመጣሁት፡፡ ስለገንዘብና ሀብትም አልነበረም፡፡ አገር ውስጥ ሠርቶ መኖር ነው ወደዚህ ያስመጣኝ ጉዳይ፡፡

እርግጥም በኢንቨስትመንቱ መስክ የተፈጠረውን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም ውጤታማ የሚባሉ ሥራዎችን ለማከናወን ረጅም ጊዜ አልፈጀብኝም፡፡ ወደ አገሬ ተመልሼ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴዬን የጀመርኩት ‹ሮያል ክራውን› የተባለውን የማዕድን ውኃ በጥናት ላይ በተመሠረተ ሁኔታ ለማምረትና ለገበያ በማቅረብ ነው፡፡ በኢንቨስትመንት ሥራዎቼ አዳዲስና ፈር ቀዳጅ የሆኑ ተግባራትን ለማከናወንና ውጤታማነቴን ለማስመስከር የቻልኩት ግን፣ ነገሮች ሁሉ ቀና ሆነውልኝና እንቅፋት ሳይገጥመኝ ቀርቶ አይደለም፡፡ ከጅማሬዬ አንስቶ እስከ ሰሞኑ የስም ማጥፋት ዘመቻ የተንኮልና የሴራ ገመድ እየተሸረበብኝ፣ እየወደቅኩና እየተነሳሁ እዚህ መድረሴን አገር የሚያውቀው ጉዳይ ነው፡፡ ‹ሮያል ክራውን› የተባለውን የማዕድን ውኃ እያመረተ ለገበያ የሚያቀርበውን ኩባንያ አቋቁሜ በአጭር ጊዜ ውስጥ ትርፋማ መሆኔ ያንገበገባቸው ሴረኞች፣ በአደባባይም በስውርም ሊያጠምዱኝ ብዙ ለፍተዋል፡፡ እናም ተሳክቶላቸዋል፡፡

ወደ ገበያ በገባ መንፈቅ ባልሞላ ጊዜ ውስጥ፣ የአዲስ አበባን የማዕድን ውኃ ገበያ 60 በመቶ ድርሻ መያዝ የቻለው ሮያል ክራውን ከገበያ ለማስወጣት ብዙ ተንኮል ተሠርቶብኛል፡፡ ‹‹ሮያል ክራውን የሽንት ቤት ውኃ ነው›› የሚል የሐሰት ወሬ በመንዛት ደንበኛን በማደናገር የተጀመረው የስም ማጥፋት ዘመቻ፣ ቀስ በቀስም እንዲህ እንደ ሰሞኑ በጋዜጣም ተፋፋመብኝ፡፡ አንድ ቀን፣ የግሉ ፕሬስ ጋዜጠኛ መሆኑን የገለጸ ግለሰብ ወደ ቢሮዬ በመምጣት ‹‹ሮያል ክራውን የሽንት ቤት ውኃ መሆኑን የሚገልጽ ዘገባ እንድሠራ የተወሰኑ ግለሰቦች ገንዘብ ሰጥተውኛል፡፡ እኔ ግን ነገሩ እርስዎን የሚጎዳ መሆኑን በማመን ጉዳዩን ልነግርዎትና መፍትሔ እንዲፈልጉ ላስገነዝብዎት ነው የመጣሁት፡፡ አምስት ሺሕ ብር የሚሰጡኝ ከሆነ ዘገባውን አልሠራም፤›› የሚል ሐሳብ አቀረበልኝ፡፡ በወቅቱ የሰጠሁት ምላሽ ‹‹አምስት ሺሕ ብር ይቅርና አሥር ሳንቲም አልሰጥህም፡፡ የፈለከውን መሥራት ማድረግ ትችላለህ፤›› የሚል ነበር፡፡

ይኼን ተከትሎ ነው እንግዲህ በተከበረው የጋዜጠኝነት ሙያ ስም ርካሽ ጉርሻ ፍለጋ የሚባዝኑ ‹ስመ ጋዜጠኞች› በሠሩብኝ ሐሰተኛ ዘገባ ሮያል ክራውን በኪሳራ ውስጥ መዘፈቅ የጀመረው፡፡ በዚህ ሐሰተኛ ዘገባ ሰበብ ኢንቨስትመንቴ አደጋ ላይ ቢወድቅም፣ እኔ ግን ተስፋ ባለመቁረጥና እጅ ባለመስጠት ከአደጋው ለማምለጥ የተቻለኝን ከማድረግ አልተቆጠብኩም፡፡ ይኼም ሆኖ ግን ውጭ ውጩን የተከፈተብኝ የማጥፋት ዘመቻ ኩባንያዬ ውስጥ ሥር ሰዶ በመግባት በአንዳንድ የኩባንያው ሠራተኞችና አመራሮች አማካይነት ኢንቨስትመንቴን በስውር መገዝገዝ ቀጥሎ ነበርና ሮያል ክራውን እንዳይነሳ ሆኖ ወደቀ፡፡ በስተመጨረሻም የቤት መኪናዬን ሸጬ ለሠራተኞቼ ደመወዝ በመክፈል ፋብሪካውን ለመዝጋት ተገደድኩ፡፡ የሮያል ክራውን ስኬታማ ጉዞ በሴረኞች ተንኮል ተደናቅፎ በአጭሩ ቢቀጭም፣ እኔ ግን ተስፋ አልቆረጥኩም፡፡ ከወደቅኩበት ተነስቼ በሌላ መንገድ ረጅም ጉዞ እንደማደርግ ቅንጣት ያህል ጥርጣሬ አልነበረኝም፡፡ ለዚህም ነው እንደገና ለመነሳትና በአገሪቱ የመጀመሪያው የሆነውን ‹ሃይላንድ› የተሰኘ የታሸገ ንፁህ ውኃ ለማምረት የቻልኩት፡፡ ከኪሳራ በመውጣት ሃይላንድ ውኃን ለገበያ በማቅረብ በአጭር ጊዜ ውስጥ ትርፋማ ሥራ ማከናወን ብቀጥልም፣ አሁንም ግን የምቀኞች ሴራና ጠልፎ የመጣል ዘመቻ ከእኔ አልራቀም፡፡

እኔ የአዳዲስ የኢንቨስትመንት መስኮችን በመቀየስ በሥራ ተጠምጄ ጉዞዬን ስቀጥል፣ ሴረኞችም ዱካዬን እየተከተሉ አዳዲስ የጥቃት ስልቶችን በመቀየስ ጠልፎ የመጣል ዘመቻውን ገፉበት፡፡ ከዚህ በኋላም ቢሆን ዘመቻው ተጧጡፎብኝ ነው በኢንቨስትመንት መስክ ርቄ የተጓዝኩት፡፡ ከሁለት በላይ ድርጅቶቼ በምቀኞች ሴራና ጠልፎ የመጣል ዘመቻ ለኪሳራ ተዳርገው ቢዘጉብኝም፣ በተንኮልና ደባ ላለመሸነፍ በመቁረጥ ባለፉት 17 ዓመታት ሲደረጉብኝ የነበሩ ተደጋጋሚ ጠልፎ የመጣል ሙከራዎችን እየተጋፈጥኩ፣ በኢንቨስትመንቱ መስክ ውጤታማ ሥራዎችን አከናውኛለሁ፡፡ በእነዚህ ሁሉ ዓመታት ያደረግኳቸው የኢንቨስትመንት ሥራዎች አገርንና ወገንን የሚጠቅሙ፣ አዳዲስና ዘመናዊ አሠራሮችን የሚያስተዋውቁና ዘርፉን የሚያሳድጉ ናቸው፡፡

ከእነዚህ ተጠቃሽ ሥራዎች መካከል ከሦስት ሺሕ በላይ ባለአክሲዮኖችን በማሰባሰብ በከፍተኛ መስዋዕትነት ያቋቋምኩትና በቦርድ ሰብሳቢነት በመምራት በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ትርፋማነት ያሸጋገርኩት ዘመን ባንክ ይጠቀሳል፡፡ ዘመን ባንክን የማቋቋምና የማደራጀት ሥራዬን በጀመርኩበት ወቅት የገጠሙኝን ፈተናዎች ለመግለጽ ቃላት ያጥሩኛል፡፡ በአንድ በኩል ይዤው የመጣሁት አዲስ ዓይነት የባንክ አሠራር ፍፁም ሊሳካ የማይችል ተደርጎ መተቸትና ባለአክሲዮኖች እንዳይቀላቀሉ የመገፋፋት ሥራ ሲሠራ፣ በሌላ በኩል ደግሞ ባንኩን በሕጋዊ መልኩ የማቋቋም ሒደቱ አግባብ ባልሆነ ጣልቃ ገብነትና እንቅፋት ከአንድ ዓመት ከመንፈቅ በላይ ተጓቷል፡፡ ይኼም ሆኖ ግን አይሳካለትም ተብሎ ሲተችና ወደ ሥራ እንዳይገባ እንቅፋት ሲፈጠርበት የቆየው ዘመን ባንክ፣ ወደ ሥራ በገባ በአጭር ጊዜ ውስጥ ነው ብዙዎችን አጀብ ያስባለና ሐሜተኞችንና ተቺዎችን ያሳፈረ ውጤት ማስመዝገብ የቻለው፡፡ ፍፁም ቅዠት የተባለለትን በአንድ ቅርንጫፍ ብቻ የመሥራት ዕቅድ ተግባራዊ ማድረግ የጀመረው ባንካችን፣ በአገሪቱ ለረጅም ዓመታት አገልግሎት ሲሰጡ ከቆዩ አርባና ሃምሳ ቅርንጫፎች ያሏቸው ነባር ባንኮች እኩል ውጤታማ ሥራ የሠራው በአንድ ቅርንጫፍ ብቻ ነው፡፡

ዘመን ባንክ ይዞት የመጣው አዲስና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደራጀ ቀልጣፋ የባንክ አሠራር እንደተተቸው የማይሳካ አለመሆኑን አረጋግጧል፡፡ አሠራሩን ይተቹ የነበሩ በባንኩ ኢንዱስትሪ ውስጥ የነበሩ ባለሙያዎች፣ የዘመን ባንክን ውጤታማነት ሲመለከቱ ትችታቸውን ትተው አሠራሩን በራሳቸው ባንክ መተግበር የጀመሩት ጥቂት ቆይተው ነው፡፡ ዘመን ባንክ እንደ ተቋም ትርፋማ ከመሆንና ባለአክሲዮኖቹን ተጠቃሚ ከማድረግ ባለፈ ለአጠቃላዩ የአገሪቱ የባንክ ኢንዱስትሪ ወደተሻለ ደረጃ ከፍ ማለት የራሱን የሆነ ጉልህ አስተዋጽኦ አበርክቷል፡፡ ነባር ባንኮች አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በተፋጠነ ሁኔታ ተጠቃሚ የሆኑትና ቀልጣፋና ዘመናዊ የባንክ አሠራሮችን ማስፋፋት የጀመሩት የዘመን ባንክን ፈር በመከተል ስለመሆኑ ሁሉም የሚያውቀው ነው፡፡ ሌላው ይቅርና ባንኮች በተወሰነ ሰዓት አገልግሎት መስጠታቸውን ትተው የምሳ ሰዓት እረፍትን ማስቀረትና እስከ ምሽቱ ሦስት ሰዓት ደንበኞችን ማስተናገድ የጀመሩት የዘመን ባንክን አሠራር እንደ መልካም ተሞክሮ በመውሰድ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በአገሪቱ የባንክ ኢንዱስትሪ ውስጥ ትልቅ ለውጥ የፈጠረውን ዘመን ባንክ ወደ ትርፋማነት በማሸጋግርበት ወቅት ግን ብዙም ሳይቆይ እሱም የሴረኞች ደባ ሰለባ መሆን ጀመረ፡፡

የባንኩን የቦርድ ሰብሳቢነት ቦታ ለመንጠቅና የግል ጥቅማቸውን ለማጋበስ የቋመጡ ጥቂት ግለሰቦች አሁንም የተለመደ አሉባልታቸውን በመንዛት ጉዞዬን ለማደናቀፍ በስውር ማድባት ያዙ፡፡ እኔን ተጠያቂ ለማድረግና የባንኩን አመራርነት ለመረከብ የቋመጡት እነዚህ ግለሰቦች፣ መሠረት የሌለው ውንጀላ በመፍጠር ኢ-ፍትሐዊ በሆነ መንገድ ይከሱኝ ጀመር፡፡ ብሔራዊ ባንክም የግለሰቦቹን መሠረተ ቢስ ጥቆማ በመቀበል እኔን ከባንኩ በቦርድ አባልነት አገደኝ፡፡ ውሳኔው አግባብነት የሌለው እንደሆነ በመጥቀስ ለብሔራዊ ባንክ ቅሬታና አቤቱታዬን አቅርቤ መልስ በምጠባበቅበት ወቅትም የዘመን ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ምርጫ በግዴታ እንዲከናወን ተደረገ፡፡ እኔ በታገድኩበት ሁኔታ ምርጫው እንዲካሄድ ተደርጎ ነው እንግዲህ እነዚያ ለሥልጣንና ለግል ጥቅም የቋመጡ ግለሰቦች የአመራርነት ቦታውን የያዙት፡፡ እውነት ለመናገር በዚህ ወቅት የወለድኩትን ልጅ የመነጠቅ ያህል ስሜት ነው የተሰማኝ፡፡ ከመነሻውም የሥራ እንጂ የሥልጣን ጥም የለኝምና ይኼን ጉዳይ ችላ በማለትና ሙሉ ትኩረቴን ሥራ ላይ በማድረግ ወደፊት መጓዜን ቀጠልኩ፡፡ ይኼም ሆኖ ግን አሁንም ግለሰቦቹ የጠነሰሱት ሴራ ከዘመን ባንክም አልፎ በሌሎች የኢንቨስትመንት ሥራዎቼ ላይም ኢ-ፍትሐዊ በሆነ መንገድ እንቅፋት መፍጠሩ አልቀረም፡፡

ጥር 17 ቀን 2004 ዓ.ም. በአጠቃላይ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴዬና በቀጣይ ዕቅዴ ላይ ከፍተኛ የሆነ አሉታዊ ተፅዕኖ የሚፈጥር፣ አግባብነት የሌለው ውሳኔ በብሔራዊ ባንክ ተላለፈብኝ፡፡ ዘመን ባንክን ጨምሮ በየትኛውም የፋይናንስ ተቋም ውስጥ የቦርድ አባል እንዳልሆን፣ ዘመን ባንክም እኔ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ባለቤት ለሆንኩባቸው ወይም በቦርድ አባልነት ወይም በዋና ሥራ አስፈጻሚነት ለማስተዳድራቸው ድርጅቶች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ማናቸውንም ዓይነት አዲስ ብድር እንዳይሰጥ፣ ወይም ከዚህ በፊት የተሰጡኝን ብድሮች እንዳያድስ የሚያዝዘው ይህ ውሳኔ፣ እርግጥም ከኢንቨስትመንት ሜዳው ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንድወጣና ተስፋ ቆርጬ ወደውጭ አገር እንድሰደድ የሚያስገድድ ነበር፡፡ ሴረኞች በፈጠሩት መሠረተ ቢስ ጥቆማ ተንተርሶ የተላለፈብኝ ይህ ውሳኔ፣ ቢአንቨስትመንት መስኩ ለዓመታት ብዙ መስዋዕትነት ከፍዬ የገነባሁትን መልካም ስምና ዝናዬን ጥላሸት የሚቀባ፣ በፓርተነሮቼ፣ በመንግሥት አካላት፣ በደንበኞቼና በመላው ሕዝብ ዘንድ ያሰረፅኩትን አመኔታ የሚያሳጣኝ፣ ቀጣይ ሰፋፊ የኢንቨስትመንት ዕቅዶቼን የሚያሰናክል ነበር፡፡ ይህም ሆኖ ግን አንዳች የተስፋ መቁረጥ ስሜት አልተፈጠረብኝም፡፡ በየመንገዴ ላይ ተደቅነው በሚጠብቁኝ የሴረኞች እንቅፋት እየተጠለፍኩ፣ እየወደቅኩ፣ እየተነሳሁ፣ እየተጓዝኩ፣ እንዲህ እንዲህ እያልኩ… በውጣ ውረድ የታጀበ የኢንቨስትመንት ጉዞዬን ገፋሁበት፡፡ በዚህ ሁኔታ ለ17 ዓመታት የዘለቀውና ወደፊትም ተጠናክሮ የሚቀጥለው የኢንቨስትመንት ጉዞዬ ነው እንግዲህ ‹የሕዝብ ብር ዘርፎ በመጥፋት ተጠናቀቀ› ተብሎ ከሰሞኑ መታማት የጀመረው፡፡ ‹በኢትዮጵያ ኢንቨስት ማድረግ› የሚል መርህ ባለው አክሰስ ካፒታል ሥር የሚገኘው አክሰስ ሪል ስቴት፣ የሕዝብን ገንዘብ ዘርፎ ከኢትዮጵያ ውጭ መሰደዱ ተዘገበ፡፡ በተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮች ሰፋፊ ሥራዎችን ሲያከናውን የቆየው የአክሰስ ካፒታል ከሴረኞች ምላስ በሚረጭ የወሬ መርዝ መቆሸሽ ያዘ፡፡

በሺሕዎች የሚቆጠሩ ቋሚ ሠራተኞችን የሚያስተዳድረውና ወደ አንድ ሺሕ ባለአክሲዮኖች ያቋቋሙት፣ በዓመት ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ ለመንግሥት ግብር የሚያስገቡ፣ ሕጋዊ ሆኖ ተቋቁመው ሕጋዊ ሥራ የሚሠሩት የአክሰስ ግሩፕና ሌሎችም እኔ ያቋቋምኳቸው ድርጅቶች እንደ ‹ማፍያ ቡድን› ተቆጠሩ፡፡ አዳዲስ የቢዝነስ ሐሳብ በማመንጨት፣ በሺሕዎች የሚቆጠሩ ባለአክሲዮኖችን በማደራጀት፣ ለሕዝብና ለአገር የሚጠቅሙ ፈር ቀዳጅ ኢንቨስትመንት ሥራዎችን በማቋቋም ለ17 ዓመታት ደፋ ቀና ሲል የነበረው ኤርሚያስ አመልጋም፣ ‹በአክሰስ ሪል ስቴትም ስም ከሕዝብ የሰበሰበውን ብር በግል ካዝናው አጭቆ ተሰወረ› ተባለ፡፡ ይህ አሉባልታና ወሬ የእኔን የኤርሚያስ አመልጋን ‹ስም› እንጂ፣ ‹እውነት› እንደማያጠፋው አውቃለሁ፡፡ ይህን መሰሉን ጠልፎ የመጣል ሴራ አውቀዋለሁም ለምጄዋለሁም፡፡ ስለማውቀውና ስለለመድኩት ችላ ብዬ ልተወው አስቤ ነበር፡፡ ችግሩ ግን አሉባልታው እንደወትሮው በግለሰቡ ‹ኤርሚያስ› ላይ ብቻ ሳይሆን፣ በተቋሙ ‹አክሰስ› ላይም የተቃጣ መሆኑ ነው፡፡ ከሰሞኑ እየተናፈሰ ያለው ወሬ እኔን ብቻ የሚመለከት አይደለም፡፡ ብዙ የኩባንያው ባለ አክስዮኖችን፣ በሺሕዎች የሚቆጠሩ ሠራተኞችን፣ ደንበኞችን ብሎም መላውን ሕዝብ የሚያሳዝን ነው፡፡ ለዚህም ነው ወሬውን እንደተራ ወሬ ችላ ብዬ ለማለፍ ያልፈለግኩት፡፡ ዘመቻው የኔንና የአክሰስን ‹ስም› እንጂ ‹እውነት› የማጥፋት አቅም የለውም፡፡

ሰሞነኛውን የአሉባልታ ወሬ ይዞ የመጣው ንፋስ ሲያልፍ፣ እውነት ቁልጭ ብሎ እንደሚወጣ አውቃለሁ፡፡ ይኼም ሆኖ ግን ንፋሱ ይዞት የመጣው የወሬ ገለባ በብዙዎች ዓይን ገብቶ በአክሰስም ሆነ በእኔ ላይ የተዛባ አመለካከት የመፍጠር አቅም ያለው መሆኑን በመገንዘብ፣ ለጊዜውም ቢሆን ስለማይፋቀው ‹እውነት› ጥቂት ግንዛቤ መስጠት ይኖርብኛል፡፡ አክሰስ ‹የማፍያዎች ቡድን› ኤርሚያስ ‹የቡድኑ መሪ› አይደሉም፡፡ አክሰስ ሕጋዊ መሠረት ጠብቆ የተቋቋመና መንግሥት የሚያወጣቸውን የልማት ፖሊሲ፣ ስትራቴጂና መመርያዎች በማክበር ለልማቱ መፋጠን ጉልህ ሚና በመጫወት ላይ የሚገኙ በተለያዩ ዘርፎች የተሰማሩ ድርጅቶችን በሥሩ የያዘ ሕጋዊ ኩባንያ ነው፡፡

እንደ ዘመን ባንክ ሁሉ ሌሎች የኢንቨስትመንት ሥራዎቼም በአገሪቱ ፈር ቀዳጅና ለየሴክተሩ ዕድገትና ትራንስፎርሜሽን የራሳቸውን አዎንታዊ ሚና የተጫወቱ እንዲሁም የቴክኖሎጂ ሽግግር በመፍጠር ረገድ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ስለመሆናቸው ሁሉም የሚመሰክርላቸው ናቸው፡፡ የማመነጫቸው የቢዝነስ ሐሳቦች ወደ መጀመሪያ ላይ ሁሌም የማይሳኩ ተብለው የሚተቹ ቢሆኑም በጥናት ላይ ተመሥርተው ወደ ተግባር ሲለወጡ ግን ውጤታማና ለሌሎች ኢንቨስተሮች መነሻ የሚሆኑ ፈርቀዳጅ ኢንቨስትመንቶች ወደመሆን ያመራሉ፡፡ የአባባሌን እውነታነት ለማረጋገጥ የሃይላንድን ተሞክሮ መመልከት ብቻ በቂ ይመስለኛል፡፡ በአገሪቱ ውኃን በፕላስቲክ ጠርሙሶች አሽጎ ለመሸጥ ማሰብ እንደ እብደት ያስቆጥር በነበረበት ዘመን፣ ወደ ገበያ ይዤው የወጣሁትና በስፋት መሸጥ የጀመረው ሃይላንድ፣ ‹ውኃ አሽጎ መሸጥ› የሚል አዲስ ኢንቨስትመንት ለአገሪቱ ማስተዋወቁን ሁሉም የሚያውቀው ጉዳይ ነው፡፡ ከዓመታት በፊት ሃይላንድ የቀደደውን ቦይ ተከትለው ነው ሃያ ስምንት ያህል ውኃዎች ወደ ገበያው የፈሰሱት፡፡

የኢንቨስትመንት ሐሳቦቼን ፈርቀዳጅነትና ለአጠቃላዩ የአገሪቱ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ትራንስፎርሜሽን የሚያበረክቱትን አዎንታዊ ሚና የሚያሳየው ሌላው ተጠቃሽ ነገር ደግሞ፣ ወደ አገሬ ከተመለስኩ በኋላ በነበሩት የመጀመሪያዎቹ ዓመታት በሌሎች አገሮች በስፋት የሚሠራበትንና ለኢንቨስትመንት ማደግ ጉልህ ሚና የሚጫወተውን የአክሲዮን ሽያጭ አሠራር ለማስተዋወቅና በአገሪቱ እንዲጀመር ለማድረግ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ያደረግኩት ጥረት ነው፡፡ ምንም እንኳን የአክሲዮን ገበያ የማቋቋም ጅምሬ በተለያዩ እንቅፋቶች ምክንያት ሊሳካ ባይችልም፣ የአክሲዮን ሽያጭ በማሰባሰብ ሰፋፊ ኢንቨስትመንትቶች የሚያከናውን ኩባንያ በማቋቋም ፈርቀዳጅ ሥራ ሠርቻለሁ፡፡ ከዓመታት በፊት በዚህ ሁኔታ የጀመርኩትና ለአገሬ ያስተዋወቅኩት የአክሲዮን ሽያጭ አሠራር፣ አሁን አሁን በስፋት ተግባራዊ እየተደረገና በዚህ አሠራር አማካይነትም በርካታ ቁጥር ያላቸው የአክሲዮን ማኅበሮችና ኩባንያዎች እየተመሠረቱ ለኢንቨስትመንቱ መፋጠን የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እያበረከቱ ይገኛሉ፡፡

ከግል የኢንቨስትመንት ሥራዎቼ ባለፈ ለሴክተሩና ለአገር ዕድገት ያበረከትኳቸው እነዚህና ሌሎች እውነታዎች ተሽረው ነው እንግዲህ የግል ጥቅሜን ለማሳደድ ደፋ ቀና ስል የኖርኩ ስግብግብና ኃላፊነት የማይሰማኝ ተራ ነጋዴ ስለመሆኔ አሉባልታ ይሰራጭብኝ የጀመረው፡፡ ስለራሴ መናገር አይሁንብኝና በኢንቨስትመንት ሥራዎቼ ለግሌ ካካበትኩት ሀብት ይልቅ ሌሎችን ተጠቃሚ ማድረጌና አገሬን መጥቀሜ የበለጠ ዋጋ አለው፡፡ ይህ እውነታ ተሽሮ ነው እንግዲህ አክሰስ የዝርፊያ ቡድን እንደሆነ ተደርጎ መወራት የጀመረው፡፡ አክሰስ ግን እንዲህ ሐሜተኞች እንደሚሉት አይደለም፡፡ ኩባንያው ከሦስት ሺሕ በላይ ለሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል የፈጠረ፣ በዓመት ከመቶ ሚሊዮን ብር በላይ ግብር ለመንግሥት የሚያስገባ፣ በበርካታ ባለአክስዮኖች ተቋቁሞ በጠንካራ ቦርድ የሚመራ ተቋም እንጂ፣ አንድ ኤርሚያስ ለዝርፊያ ያቋቋመውና ዘርፎ ዘርፎ ሲበቃው በትኖት የሚሄደው የልጆች ዕቃ ዕቃ ጨዋታ ማኅበር አይደለም፡፡ ኤርሚያስም ዘርፊያን ዓላማው በማድረግ ከአሜሪካ መጥቶ ባቋቋመው የማፊያ ቡድን ስም ከባለ አክስዮኖችና ከሕዝቡ የሰበሰበውን ብር ይዞ በስውር ወደ አሜሪካ የሚያመልጥ ‹ነጣቂ› አይደለም፡፡ ለመሠረተ ቢሱ ሐሜትና አሉባልታ መነሻ የሆነው አክሰስ ሪልስቴት በቅርቡ በዚሁ ጋዜጣ ላይ እንደገለጽኩት በቤቶች ልማት ዘርፍ ተጠቃሽ ሥራ የመሥራት እንጂ ከደንበኞች የሰበሰበውን ገንዘብ ይዞ የመሰወር ዓላማ የለውም፡፡ ባጋጠሙን የተለያዩ ውስጣዊና ውጫዊ ችግሮች ሰበብ ያሰብነውን ያህል ሥራ ማከናወን አለመቻላችንን አምናለሁ፡፡

ደንበኞች ችግሩን ተረድተው ከኩባንያው ጋር ያላቸውን ግንኙነት እንዲቀጥሉ ለማድረግ ጥረት አድርጌያለሁ፡፡ እንደ ኩባንያው አመራርነቴ የተከሰቱ ችግሮችን ለመፍታትና የተጓተቱ ሥራዎችን ለማስቀጠል በሙሉ አቅሜ በመሥራት ላይም እገኛለሁ፡፡ ይኼም ሆኖ ግን መሠረተ ቢስ አሉባልታ ማናፈስ የጀመሩ አንዳንድ ግለሰቦች ኃላፊነቴን በመዘንጋትና ለግል ጥቅሜ በማሰብ ኩባንያውን አፈራርሼ እንደሄድኩ ማስወራት ይዘዋል፡፡ እውነቱን ለመናገር ይህንን አስጸያፊ ድርጊት ለማድረግ ዝግጁ የሆነ መንፈስ የሌለኝ ሰው ነኝ፡፡ የአክሰስ ሪል ስቴት ጉዳይ ከአሁን በኋላ ለእኔ የኢንቨስትመንትና የቢዝነስ ሳይሆን የሕይወት ጉዳይ ነው፡፡ ኩባንያውን ከገባበት የችግር አረንቋ አውጥቶ የጀመራቸውን ሥራዎች በአግባቡ እንዲፈጽም ማድረግ በሕይወት ዘመኔ ሙሉ መክፈል የሚገባኝን መስዋዕትነት በመክፈል እውን ለማድረግ የወንኩበት ታላቅ ዓላማዬ ነው፡፡ ለዓላማዬ እንጂ ለግል ጥቅሜ ቆሜ አላውቅም፡፡ ለግል ጥቅሜና ለምቾቴ የምሯሯጥ ሰው ብሆን ኑሮ ትርፋማ ቢዝነስ ያለኝ ሰው እንደመሆኔ የድሎት ኑሮን ስገፋ በታየሁ ነበር፡፡ ብዙዎችን ባለመኖሪያ ቤት ለማድረግ ደፋ ቀና የምለው እስካሁንም ድረስ የራሴ የቤት መኪና የሌለኝ፣ በአንዲት አነስተኛ የኪራይ ቤት ውስጥ የምኖር ባለሀብት ስለመሆኔ መናገር ያለብኝ አይመስለኝም፡፡

አክሰስ ሪል ስቴትን በዚህ ሁኔታ በትኖ መሄድ ለእኔ ከሽንፈትም በላይ የሆነ ራስን የማዋረድ ተግባር ነው፡፡ የአክሰስ ሪል ስቴት ጉዳይ እንደዋዛ በትኜው የምሄድ የግል ጉዳዬ አይደለም፡፡ አክሰስን አፈራርሶ በመሄድ ውስጥ ብዙ ጥፋቶችን መሥራት አለ፡፡ በሺሕዎች የሚቆጠሩ ሠራተኞቼን፣ ደንበኞቼን፣ ባለአክሲዮኖቼን፣ የቢዝነስ ፓርትነሮቼን፣ መላ ሕዝቡንና መንግሥትን አስቀይሜና የተጣለብኝን ኃላፊነት አጉድዬ ለማምለጥ መሞከር ለእኔ ሥርየት የሌለው ጥፋት ነው፡፡ ዓላማዬ የሕዝብን ገንዘብ በማጋበስ የግል ካዝናዬን መሙላት ቢሆን ኖሮ፣ እዚያው አሜሪካ ያቋቋሙኩትን ትርፋማ ድርጅቴን ዘግቼ ለመምጣት ባልወሰንኩ ነበር፡፡ ወደ አገሬ የመጣሁት የሕዝብን ገንዘብ ለመዝረፍና ተመልሼ ወደ አሜሪካ ለመኮብለል አይደለም፡፡ ተልዕኮዬ ሕዝቡን በማጭበርበር በሕገወጥ መንገድ መክበር ቢሆን ኖሮ፣ በቀላሉ ብዙ ብር ማግኘት የሚያስችሉ የማታለል ድርጊቶችን ማከናወን ይቀለኝ ነበር፡፡ እንዲህ ያለውን ርካሽ ተራ የማጭበርበር ተልዕኮ ለማስፈጸም፣ አክሰስን ያህል ግዙፍ ተቋም ማቋቋምም ሆነ በሺሕዎች የሚቆጠሩ ሠራተኞችን መቅጠርና ዓመታትን የፈጀ ረጅምና ፈታኝ ጉዞ ማድረግ ባለስፈለገኝ ነበር፡፡ እንኳን ርካሽ የማጭርበር ሥራ ይቅርና ራስን በቀላሉ ወደሚሊየነርነት መቀየር የሚያስችሉ የተለመዱ ‹ገዝቶ በመሸጥ› ትርፍ የሚያስገኙ ንግዶችን ለመሥራት ዝግጁ የሆነ መንፈስ የሌለኝ ሰው ነኝ፡፡ ባለፉት 17 ያህል ዓመታት የኢንቨስትመንት ጉዞዬ ውስጥ በቀላሉ ማትረፍ የሚያስችሉ የተለመዱ መሰል ‹ዕቃ ገዝቶ አትርፎ የመሸጥ› ሥራዎች ውስጥ እጄን አስገብቼ አላውቅም፡፡

መሰል ሥራዎች ያለብዙ ውጣ ውረድ አትራፊ እንደሚያደርጉ አውቃለሁ፡፡ ይኼም ሆኖ ግን እንደተባለው ቀላል ሥራ ሠርቶ ትርፍ የማጋበስ ህልም ስለሌለኝ፣ ትኩረቴን ያደረግኩት አዳዲስና ፈርቀዳጅ የቢዝነስ ሀሳቦችን ወደማመንጨት፣ ድካምና ውጣ ውረድ የሚጠይቁ ፈታኝ ኢንቨስትመንቶችን ወደመፍጠር፣ ከራስ ይልቅ ለአገር ልማትና ለሴክተር ዕድገት አስተዋጽኦ የሚያበረክቱና እሴት የሚጨምሩ ኩባንያዎችን ወደማቋቋምና ለስኬታማነት ወደማብቃት ነው፡፡ ይህም ዓላማዬ ከራስ አልፈው ለአገርና ለወገን የሚጠቅሙ ታላላቅ ሥራዎችን በመሥራት በፈታኝ ሁኔታ ውስጥ አልፎ በሒደት ማደግ እንጂ፣ በአቋራጭ ትርፍ አካብቶ የግል ካዝናን መሙላት አለመሆኑን በግልጽ ያሳያል የሚል እምነት አለኝ፡፡ ላቤን አፍስሼ አገሬ ውስጥ ሠርቼ ውጤታማ ለመሆን እንጂ፣ እንደተባለው ሕዝቤን ዘርፌ ወደ አሜሪካ ለመመለስ ባስብ ኖሮ የአሜሪካ መኖሪያ ፈቃዴን (ግሪን ካርዴን) አዲስ አበባ ውስጥ ለሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ በፈቃደኝነት ባልመለስኩ ነበር፡፡

በወቅቱ አዲስ አበባ ወደሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ሄጄ ካርዴን በፈቃደኝነት ለመመለስ ጥያቄ ሳቀርብ፣ የኤምባሲው ሠራተኞች በከፍተኛ መገረም እንደተቀበሉኝ አልረሳውም፡፡ በየዓመቱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች የአሜሪካ ግሪን ካርድ ፍለጋ ደጅ የሚጠኑበት የዚህ ኤምባሲ ሠራተኞች፣ ባልተለመደ ሁኔታ ተቃራኒ ጥያቄ ይዤ ወደእነሱ ስሄድ በጥርጣሬ ነበር የተመለከቱኝ፡፡ ‹‹ግሪን ካርድህን አንዴ ለኤምባሲው ከመለስክ በኋላ መልሰህ ማግኘት እንደማትችል ታውቃለህ አይደል?›› በማለት ነበር ሥጋት ገብቷቸው የጠየቁኝ፡፡ አሠራሩን እንደማውቅና ሆን ብዬ እንደማደርገው ነግሬያቸው አስፈላጊውን የማመልከቻ ቅጽ ለመሙላት ስዘጋጅ ግን የሚገርም ነገር ነበር የተከሰተው፡፡ ግሪን ካርድ ለመመለስ የሚያመለክቱ ባለጉዳዮች እንዲሞሉት በኤምባሲው የተዘጋጀው ቅጽ በቀላሉ ሊገኝ አልቻለም፡፡ ምክንያቱም ከዚህ በፊት ግሪን ካርድ ለመመለስ ያመለከተ ሰው ወደ ኤምባሲው ዝር ብሎ አያውቅም ነበር፡፡ በስንት ፍለጋ የተገኘውን ይህን ቅጽ ሞልቼ ነው ብዙዎች የሚጓጉለትን የአሜሪካ ግሪን ካርዴን ለኤምባሲው ያስረከብኩት፡፡ ይህ እውነታ ተዘንግቶ ነው እንግዲህ ከአሜሪካ የመጣሁት ለሥራ ሳይሆን ለዘረፋና በስውር ወደ አሜሪካ ተመልሶ ለመጥፋት እንደሆነ አሉባልታ መነዛት የጀመረው፡፡ የሕዝብ ገንዘብ ዘርፎ ወደ አሜሪካ ለመጥፋትና ተደብቆ ለመኖር ያቀደ ሰው በምን አግባብ ይሆን ወደ አሜሪካ የሚወስደውን ማምለጫ በር በገዛ እጁ የሚዘጋው? ለመሸሽ የተዘጋጀ ሰው የሚሸሽበትን በር ይዘጋልን?

ግለሰቦች እንደሚያናፍሱት ሐሜት በእርግጥም የግል ጥቅሜን ለማሳደድ የምሮጥ ሰው ብሆን ኖሮ የማይገባኝን የሕዝብ ብር ሳይሆን የሚገባኝን በሚሊዮን የሚቆጠር የግል ብሬን ያላግባብ ስነጠቅ ‹ለምን?› ብዬ ክስ ለመመሥረት በተጣደፍኩ ነበር፡፡ ለሥራ እንጂ ለግል ጥቅም የምተጋ ሰው ባለመሆኔ ይመስለኛል ‹የዘመን ባንክ የመመሥረቻ ጽሑፍና መተዳደሪያ ደንብ እንዲሁም የአገሪቱ የንግድ ሕግ በሚፈቅደው መሠረት እንደባንኩ መሥራችነቴ ሊከፈለኝ ይገባ የነበረውን 10 በመቶ የትርፍ ድርሻ ተከለከልኩ› ብዬ ተጣድፌ ሙግት ያልወጣሁት፡፡ የዘመን ባንክ ባለ አክሲዮኖች ባደረጉት 3ኛ መደበኛና 2ኛ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባዔ ያፀደቁትና የባንኩ የቦርድ አባላትም እንዲከፈለኝ በቃለ ጉባዔ ያሰፈሩት ከዘጠኝ ሚሊዮን ብር በላይ (አሁን ወደ 15 ሚሊዮን ብር ደርሷል) የትርፍ ድርሻ፣ በሴረኞች ተንኮል እንዳይከፈለኝ ሲደረግ የግል ጥቅሜን ለማስከበር ሸንጎ በወጣሁ ነበር፡፡ እኔ ግን ይህን ብር ትቼ ሥራዬን መሥራት ከቀጠልኩ ከዓመታት በኋላ ከሁለት ወር በፊት ነው ጉዳዬን ወደ ፍርድ ቤት ወስጄ ከዘመን ባንክ ብሬን ለመቀበል እንቅስቃሴ የጀመርኩት፡፡

አክሰስ ሪል ስቴት አንዳንድ አሉባልተኞች እንደሚሉት አንድ ግለሰብ በፈለገው መንገድ የሚመራውና ገንዘቡን እንደፈለገ የሚያንቀሳቅሰው፣ አልፎ ተርፎም ካዝናውን ባዶ አድርጎ የሚያስቀረው የግል ተቋም አይደለም፡፡ ይልቁንም እንደማንኛውም የአክሲዮን ኩባንያ ሕጉ የሚጠይቀውን መስፈርት ባሟላ መልኩ የተደራጀና በቦርድ የሚመራ፣ የፋይናንስ እንቅስቃሴውም ራሱን በቻለ በባለሙያዎች የተደራጀ ክፍል የሚከናወን ነው፡፡ በኩባንያው ውስጥ የሚካሄደው እያንዳንዱ የፋይናንስ እንቅስቃሴ ሕጉ የሚፈቅደውን አሠራር በተከተለ ሁኔታ በአግባቡ የሚመራ ሲሆን፣ አስፈላጊው የኦዲት ሥራ በውስጥና በውጭ ኦዲተሮች በአግባቡ እየተመረመረ ዓመታትን የዘለቀ ነው፡፡ ለመረጃ ያህል የኩባንያውን የፋይናንስ እንቅስቃሴ የሚያሳዩ ቁጥሮችን በግርድፍ ከዚህ እንደሚከተለው አቀርባለሁ፡
ከዚህ ጋር አብሮ ለግንዛቤ ያህል የአክሰስ ፕሮጀክቶች በአማካይ ግማሽ ያህል ያልተሸጡ ቤቶች እንዳሉና ከተሸጡት ውስጥም 80 በመቶ ያህሉ በክፍያ ሥርዓት እንጂ ሙሉ ካሽ ያልተከፈለባቸው በመሆናቸው በተፈራረምነው ውል መሠረት ከደንበኞቻችን የምንሰበስበው ከ700 ሚሊዮን በላይ ብር ድርጅቱ አለው፡፡ ከላይ የቀረበው ጥቅል መረጃ እንደሚያሳየው ኩባንያው በዚህ መልኩ ነው የፋይናንስ እንቅስቃሴውን በተገቢው ሁኔታ በማከናወን ላይ የሚገኘው፡፡ መሠረተ ቢሱ ሐሜት እንደሚለው ኤርሚያስ በቢሊዮን የሚቆጠር የኩባንያውን ብር ዘርፎ የሚሰደድበት ምንም ዓይነት ከፍተትም ሆነ መብት የለውም፡፡

ያለሰነድ የሚከናወን ምንም ዓይነት የገንዘብ እንቅስቃሴ ባለመኖሩ፣ በቢሊዮን የሚቆጠር ብር ይቅርና አምስት ሳንቲም ያለአግባብ ወደ ኪሴ የምጨምርበት ሁኔታ የለም፡፡ የሆነው ሆኖ በአክሲዮን ስም የሰበሰብኩት የሕዝብ ገንዘብ ነጥቄ ስለመጥፋቴ ስሜን በመጥቀስ ከሳምንታት በፊት የሐሰት ዘገባ የጻፉት ጋዜጦች ከዓመታት በፊትም ከአክሲዮኑ ጋር በተያያዘ ስሜን ጠቅሰው ዘግበው ነበር፡፡ ይህም ሆኖ ግን እነዚህ ጋዜጦች ከዓመታት በፊት በገጾቻቸው ስሜን የጠቀሱት እንደ ሰሞኑ በአክሲዮን ሰበብ ሕገወጥ ዝርፊያ ስለመፈጸሜ ሳይሆን ‹‹የአክስዮን ሽያጭ ሥራ ራሱን የቻለ ተቆጣጣሪ አካል ባለው መልኩ ሕጋዊ አደረጃጀት ይዞ ካልተቋቋመ የሕዝብን ገንዘብ ለመዝረፍ ዕድል ይፈጥራል›› በሚል ከመንግሥት አካላትና ከንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ጋር በመቀናጀት የአክሲዮን ገበያ ለማቋቋም ተጠቃሽ ሥራ ስለማከናወኔ ነው፡፡ የኢንቨስትመንት ሥራዎቼ የመንግሥትን አሠራር የሚከተሉና ልማቱን የሚደግፉ የመሆናቸውን ሀቅ መካድ የፈለጉ ሐሜተኞች፣ በቤቶች ልማት ዘርፍ የሚደረገውን እንቅስቃሴ የሚደግፍ ሥራ በመሥራት ላይ ያለው አክሰስ ሪል ስቴትን የዘራፊ ቡድን አድርገው መፈረጃቸው ሳያንሳቸው፣ ኩባንያው የመንግሥትና የልማት ጠበኛ እንደሆነ በማስመሰል የሚያናፍሱት ነጭ ውሸት ግርምትን ፈጥሮብኛል፡፡

በአክሰስ ሥር ከሚገኙ በርካታ ድርጅቶች ውስጥ አንዱ እንኳን ልማቱንና ኢንቨስትመንቱን የሚያደናቅፍና ትክክለኛውን ሕጋዊ አሠራር የሚፃረር ሕገወጥ ተግባር ፈጽሟል በሚል በመንግሥት አካላት ክስም ሆነ አቤቱታ ቀርቦበት አያውቅም፡፡ ይልቁንም የመንግሥትን የልማት እንቅስቃሴ የሚደግፉ በርካታ ሥራዎችን በመሥራት ነው የሚታወቀው፡፡ አክሰስ ካፒታል አዳዲስ የኢንቨስትመንት መስኮችን በፈርቀዳጅነት በማስተዋወቅ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ በማስገኘት፣ ለአጠቃላይ አገራዊ የኢኮኖሚ ዘርፍ ዕድገት በግብዓትነት የሚውሉ የጥናትና ምርምር ሥራዎች በመሥራትና ለመንግሥት አካላት በማቅረብ ተጠቃሽ ሥራ በመሥራት ያተፈረውን በጎ ስም ነው በሐሜት ለማቆሸሽ የተሞከረው፡፡ አክሰስ በጥናትና ምርምር ዘርፉ ለሚሠራቸው ሥራዎች ብዙ ገንዘብና በሙያው ያካበተ ልምድ ያላቸው ባለሙያዎችን በመመደብ ነው አገራዊ ጠቀሜታ ያለውን ተጠቃሽ ሥራ የሚያከናውነው፡፡ ይህ ደግሞ የአገር ባለውለታነቱን እንጂ ዘራፊነቱን አያስመሰክርም፡፡

በውጭ አገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን፣ የሌሎች አገሮች ባለሀብቶችና በዓለም አቀፍ ደረጃ ሰፋፊ የኢንቨስትመንት ሥራዎችን በመሥራት የሚታወቁ በርካታ የውጭ አገር ታላላቅ ኩባንያዎች ወደ ኢትዮጵያ መጥተው በተለያዩ የኢንቨስትመንት ሥራዎች ላይ እንዲሰማሩ የማግባባት ሥራ ማከናወኑም በወሬ ሊዳፈን የማይችል ሀቅ ነው፡፡ እርግጥ ይኼ የሰሞኑ ሁኔታ ከወሬነት አልፎ በሕይወት ዘመኔ ገጥሞኝ የማያውቅ ጫና በላዬ ላይ እንደከመረብኝ አልክድም፡፡ ይኼም ሆኖ ግን ይኼ ፈተናና ጫና የቀድሞ ብርታቴንና ፅናቴን የመሸርሸር አቅም የለውም፡፡ ፈተናውና እንቅፋቱ ዋጋው የማይተመን ትልቅ ትምህርት ሰጥቶኛል፡፡ “a blessing in disguise” እንዲሉ ነጮች፣ ይህ መጥፎ የሚመስል አጋጣሚ ጥሩ ነገሮችንም ጨምሮ ነው ይዞልኝ የመጣው፡፡ በዙሪያዬ የተፈጠረብኝ ውዥንበርና ግርግር፣ በውስጤ የሰረፀውን የበዛ ሰዎችን የማመን ባህሪዬን እንድፈትሽና በዙሪያዬ የነበሩትን ሰዎች ሁሉ በአርምሞ እንድገመግም ዕድል ሰጥቶኛል፡፡ ወዳጅ መስለው ከጎኔ ወዲያ ወዲህ ሲሉ የነበሩና ክፉ ቀን ሲመጣ ድንገት ከጠላቶቼ ተርታ ለመሰለፍ ያላመነቱ ጥቂት ግለሰቦች የመኖራቸውን ያህል፣ የአሉባልታ ማዕበል ሳያናውጣቸው በፅናት ከጎኔ የቆሙ መልካም ሰዎችንም አይቻለሁ፡፡ አክሰስ ቤት ለመግዛት ወስነው ገንዘባቸውን ካወጡና፣ በተፈጠሩ ችግሮች ምክንያት ቤታቸውን በወቅቱ መረከብ ካልቻሉ በርካታ ደንበኞች መካከል በሰሞኑ አሉባልታ ተደናግጠው ለክስና አቤቱታ የተነሱት ከአሥር በመቶ አይበልጡም፡፡

አብዛኛው ደንበኛ የአክሰስን ችግር በመረዳትና ችግሩን በጋራ ለመፍታት ከኩባንያው ጎን በፅናት የቆመ ነው፡፡ ጦር ከፈታው ወሬ የፈታው ይባላል፡፡ እርግጥም ወሬ የፈታቸው አንዳንድ ግለሰቦች በእኔም ሆነ በአክሰስ ሪል ስቴት ዙሪያ እያናፈሱ ያሉት አሉባልታ ቀስ በቀስ አገር ምድሩን ማዳረሱንና የሐሜት አጀንዳ መሆኑን አውቃለሁ፡፡ የወሬው ማዕበል ብዙዎቹን ያላግባብ ወደተሳሳተ አቅጣጫ እየወሰደ እንዳለም ይገባኛል፡፡ በዚህ ሁኔታ ውስጥም ሆኜ ዝም ማለት ደግሞ አግባብ አይመስለኝም፡፡ ቢያንስ የራሴን እውነት መግለጥና ሕዝቡም ከወሬው ማዕበል ገለል ብሎ የራሱን የጠራ ግንዛቤ እንዲያገኝ ማድረግ ግድ ይለኛል፡፡ ይህ በዙሪያዬ እየተከናወነ ያለው ውዥንብርና ግርግር ላለፉት አሥራ ሰባት ዓመታት ሲከተለኝ የኖረ ‹ጠልፎ መጣል› የተሰኘ የተለመደ ተከታታይ ድራማ መሆኑን መናገር እፈልጋለሁ፡፡ በሥራዎቼ የሚቀኑ ግለሰቦች፣ ተወዳድረው ማሸነፍ የተሳናቸው ደካማ ተፎካካሪዎች፣ የግል ጥቅማቸውን ለማሳደድ የሚተጉ ስግብግቦች፣ ለሥልጣን የቋመጡ ጥመኞችና ተባባሪዎቻቸው በጋራ የሚያዘጋጁት ይህ ድራማ አሁን አይደለም የጀመረው፡፡

ድራማው ከተራማጅ ዘይት ፋብሪካ ጀምሮ ወደ ሮያል ክራውን፣ ወደ ሃይላንድ፣ ወደ ዘመን ባንክ እየተሸጋገረ አክሰስ ሪልስቴት ላይ የደረሰና ላለፉት 17 ዓመታት ሲታይ የኖረ፣ በእኔ ዙሪያ የተቀነባበረ ተከታታይ ድራማ ነው፡፡ አዘጋጆቹ ይህ ድራማ ከሰሞኑ ኤርሚያስ ብር ዘርፎ ጠፋ በሚል አሳፋሪ መደምደሚያ መጠናቀቁን እየተናገሩ ነው፡፡ እኔ ግን ድራማው ገና አልተጠናቀቀም እላለሁ፡፡ የ‹ጠልፎ መጣል› ድራማውን ከቅርብም ሆነ ከሩቅ አይታችሁና ሰምታችሁ ልባችሁ የተነካ የአገሬ ሰዎች፣ በእኔ ላይ እምነት ጥላችሁ ቤት ለመገንባት በማሰብ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ብር ያወጣችሁና ባዶ እጃችንን ቀረን ብላችሁ ያዘናችሁ ደንበኞቼ፣ አብረን ሠርተን አብረን እናድጋለን ብሎ ሲያበረታታን ቆይቶ ጥሎን ጠፋ ብላችሁ የታዘባችሁ ሠራተኞቼ፣ ዓላማዬን ደግፋችሁ ከጎኔ የተሰለፋችሁ ባለአክስዮኖች፣ ወዘተ ሁላችሁም አንድ እውነት ልላክላችሁ፡፡ እየተባለ ያለው ነገር ሁሉ ፍፁም ቅጥፈት ነው፡፡ ከሚገባው በላይ እርግጠኛ ሆኜ የምነግራችሁ የጀመርነው ጉዞ እንዲህ እንደሚወራው በክህደትና በስደት የሚጠናቀቅ አይደለም፡፡ ተስፋችሁን፣ እምነታችሁን፣ ገንዘባችሁን፣ ሕልማችሁን፣ ወዘተ የሰጣችሁኝን ሁሉ ይዤ በስውር ስለመጥፋቴ ስትሰሙ፣ ለቅጽበት እንኳን ልባችሁ ወሬውን ለማመን ዝግጁ እንዳይሆን፡፡ ኤርሚያስ ሁሉንም በትኖ እዚያው አሜሪካ ይቀራል ብላችሁ እንዳታስቡ፡፡ እንኳንስ አገር ጥሎ የሚያስኮበልል ወንጀል ሳልፈጽም ቀርቶ፣ እንኳንስ በፍርኃት የሚያርድ አደገኛ ነገር ሳይከታተለኝ እኔ ኤርሚያስ ከመሬት ተነስቼና ከንቱ ሐሜትን ፈርቼ የምሸሽ ሰው አይደለሁም፡፡ በፊትም እንደምለው ዛሬም እላለሁ.. ሺሕ ዓመት እንደ አይጥ ከመኖር፣ አንድ ቀን እንደ አንበሳ ኖሮ መሞት ይሻላል!!

በአክሰስ ሪል ስቴት ላይ የተከሰተው ችግር ከአቅሜ በላይ ሆኖ ቢያስቸግረኝና በሕግ የሚያስጠይቀኝ ቢሆን እንኳን (ለነገሩ አይሆንም) ተጠያቂነትን ሸሽቼ አሜሪካ ውስጥ እንደ አይጥ ተደብቄ ለመኖር በፍፁም አልሞክርም፡፡ እዚያው አገሬ ወህኒ ወርጄ በእስር ስማቅቅ እኖራለሁ እንጂ፣ ከተጠያቂነት ለማምለጥ አሜሪካ ውስጥ አላደፍጥም፡፡ ባለፉት 17 ዓመታት ያጋጠሙኝን ተስፋ አስቆራጭ መሰናክሎች ለማለፍ የወሰድኩት ቁርጠኝነት ዛሬም ከእኔው ጋር መሆኑን እፈልጋለሁ፡፡ የማይታለፍ ቢሮክራሲዎችን ማለፍ፣ አደገኛ ጉድጓዶችን መሻገር፣ የተሸረቡ የሴራ ገመዶችን የመበጣጠስ ብቃቴ አሁንም አብሮኝ አለ፡፡

ሁሉንም ለመጋፈጥ እንጂ፣ ሸሽቶ ለማምለጥ የሚያስብ ልብ የለኝም፡፡ ምንም እንኳን በአክሰስ ላይ ተለኩሶ የሰነበተው የአሉባልታ እሳት እንደ አጀማመሩ ከፍተኛ ጥፋት የማድረስ አቅም የነበረው ቢሆንም፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ ግን እየከሰመና እየጠፋ መጥቷል፡፡ በአክሰስ ሪል ስቴት ዙሪያ ተጠምጥሞ የነበረው የችግር ካቴናም ቀስ በቀስ በሚገርም ሁኔታ ራሱን በራሱ እየፈታ መሆኑን ሳበስር በታላቅ ደስታ ነው፡፡ በሰሞኑ አሉባልታና ውዥንብር የተደናገጡ፣ ግርታና ጭንቀት የተፈጠረባቸው፣ በኩባንያውም ሆነ በእኔ ላይ ያዘኑና ደንበኞች ወደ ኩባንያችን አቅንተው እውነታውን በመረዳት ችግሮችን ፈትቶ ጅምር ሥራውን ለማስቀጠል በሚደረገው ጥረት ውስጥ ተሳታፊ ለመሆን እየተንቀሳቀሰ ነው፡፡ እንደማስበውና ሁኔታዎች እንደሚያሳዩት ችግሮቹ በአጭር ጊዜ መፍትሔ ያገኛሉ፡፡ ይህ ሆነም አልሆነም ተመልሼ ኃላፊነቴን እወጣለሁ የጀመርኩትን ሥራም እጨርሳለሁ፡፡ በሰላም ያገናኘን፡፡
የእናንተው ኤርሚያስ አመልጋ

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s