ሁለት የመከራና የድል ዓመታት (ስለሺ ሐጎስ)

2 yearsጸሀዩ(ጠራራው) መንግስታችን ማብረጃውን ይላክለትና ይኸው፡-
ሀገር አልባ ካረገኝ ሀያ ሁለት ዓመቱ
ወደብ አልባ ካረገኝ ሀያ  ዓመቱ
ፕሬስ አልባ ካረገኝ ሰባት ዓመቱ
ሚስት አልባ ካረገኝ ደግሞ ዛሬ ሁለት ዓመት ሞላው፡፡
ግን አለሁ፤ ያውም በተስፋ፤ ከማለዳ ጸሀይ እጅጉን በፈካ ተስፋ እየኖርኩ ነው፡፡
አንድ ቀን ባለ ሀገር እሆናለሁ እያልኩ ስደትን እርም ብያለሁ፤
አንድ ቀን ኤርትራ ወደ እናት ሀገሯ መመለሷን እያለምኩ የወደብ አልባነት ቁዘማዬን ትቼዋለሁ፤
አንድ ቀን ሀገሬ የነጻነት አምባ እንደምትሆን በፍጹም ልቤ በማመን ልሳናቸው ስለተዘጉ ሚዲያዎቻችን መብሰልሰሌን አቁሚያለሁ፤
አንድ ቀን ርዕዮትን እውነት ነጻ እንደምታወጣት ስለማውቅ ከብቸኝነቴ ጋር እንዲህ እዘምራለሁ፡-
Dear my love,
Our vision prevails over their fear…
Our passion prevails over their power…
Our love prevails over their hate…
Celebrate our vision for freedom, passion for justice, love for humanity and፡
I do celebrate your vision for freedom, passion for justice and love for humanity.
Dear Reeyot, …. I love you!
Advertisements

2 thoughts on “ሁለት የመከራና የድል ዓመታት (ስለሺ ሐጎስ)

  1. ወዳጀ ስለሽ በማለዳው ከእንቅልፍ ተነስቸ ያነበብኳት እጥር ምጥን ያለችው ማስታዎሻህ ልቤን በሃዘን ሊተሰሰብረው ስትታገል በመዝጊያው ያስቀመጥከው ተስፋ ተስፋ አድርጌ ልቤ ጸና ! አዎ አንተ እንደ ቅርብ አጋር ጓደኛ ከነ ቤተሰቧ የመለየት ጉዳቱ ተጠቂ ብትሆኑም የትንታጓ ወጣት እህት የርዕዮት መለየት የጎዳው ድፍን ኢትዮጵያን የሚወደውን ብሔርተኛ የሃገሬ ሰው በሙሉ ስለመሆኑ ጥርጥር የለኝም። ጋዜጠኛ ርዕዮትን የማውቃት በተደጋጋሚ ትጽፋቸው በነበሩ አስተማሪ ወኔን የተላበሱ መረጃዎቿ ነው። ጋዜጠኛ ርዕዮትን የማውቃት ባሳለፍነው አመት ባሳተመችው በኢህአዴግ በቀይ እስክርቢቶ መድበልም ነው ! ትንታጓን ርዕዮት የማውቃት እንጅ እንደ ሙያ አጋርነቴ በአካልም አይደለም ። ጋዜጠኛ ርዕዮትን በአስተማሪ ብዕሮቿ እንጅ በአካል አላውቃትም !
    አንዳንዴ የዚህችን ትንታግ ጋዜጠኛ ጉዳይ አውጥቸ አወርደውና ወደ መጨረሻው አዝናለሁ ። ከሁሉም በላይ ላለፉት ሁለት አመታት በወህኒ የደረሰባት እንግልት ፣ የተወሰደባት እና እየተወሰደባት ያለው እርምጃ ሴት እህቶች በአደባባይ ወጥተው ለሃገራቸው እድገት ፣ብልጽግናና ዲሞክራሲያዊ ስርአት መሳካት እንዳይተጉ የእልፍ አዕላፍ እህቶቸን ቅስም ሰባሪ መሆኑ ሳስበው እንኳ ያመኛል። ሴት እህቶቻችን እህቶች ከቤት እመቤትነት ከጓዳ እየወጡ መማር መመራመር ፣ የውስጥ ሃይላቸውን ማሳየትና ለሃገራቸው የሚበጀውን ለማድረግ ለፍተው ግረው ለእውነተኛ ፍትህ ድምጻቸውን ሲያሰሙ እንዲህ አይነት ፈተና ሲጋረጥባቸው ማየት አይደለም መስማቱ የቅርብ ተጠቂ የቤተሰብ አባላትን ብቻ ሳይሆን የሁላችንም ነፍስ ያቆስላል። ያም ሆኖ ከጉዳታችን እናገግም ዘንድ አለም አቀፉ ማህበረሰብ ለጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ ቆራጥ የብዕር ተጋድሎ የሰጣት ክብርና ሽልማት ነፍሳችን ከእንግልት ታድጎታል! ተስፋችን ስለእውነት ፍርድ የሚሰጠው የአምላክ ፍርድ ቢሆንም እንደ ስው በምድር ፣ በግል የሙያ አጋሬ ጋዜጠኛ ርዕዮት የንግግር ነጻነት ትግል ለከፈለችው ከሁለት አመት የዘለቀ መስዋዕትነት ከፍ ያለ ክብር እንሰጠዋለሁ! ይህም ብርታትን ይሰጠኛል!

    ለሚያልፍ ጊዜ እየተሰራ ያለው ግፍ ግን ሊቆም ይገባል!

    ቸር ያሰማን!

    ነቢዩ ሲራክ

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s