ድሪባ ኩማ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ሆኑ(ETV)

driba

አዲሱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ጉባኤ አቶ ድሪባ ኩማን የከተማዋ ከንቲባ አድርጎ ሾመ፡፡

አዲሱ ምክር ቤት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ የነበሩት አቶ አባተ ስጦታው አሁንም የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ ሆነው እንዲቀጥሉ በሙሉ ድምጽ አጸደቀ፡፡

ጉባኤው የቀድሞው ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባዔ ዶክተር ታቦር ገብረመድኅን እና ምክትል አፈ ጉባዔ አቶ ወልደገብርኤል አብርሃን በአዲሱ ምክር ቤትም በነበራቸው ስልጣን እንዲቀጥሉ መርጧቸዋል፡፡

አዲሱ ከንቲባ ድሪባ ኩማ የከተማዋን ቁልፍ ከተሰናባቹ ከንቲባ ኩማ ደመቅሳ በመረከብ  ቃለ መሃላ ፈጽመዋል፡፡

አቶ ድሪባ ኩማ የትራንስፖርት ሚኒስትር ሆነው በማገልገል የቆዩ መሆናቸው የሚታወቅ ነው፡፡

አዲሱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማ የካቢኔ አባላቶቻቸውን ለምክር ቤቱ በማቅረብም ያጸደቁ ሲሆን በዚህም መሰረት፡-

 1.  አቶ ይስሃቅ ግርማይ….የአቅም ግንባታ ቢሮ ኃላፊ

 2.  አቶ ጌታቸው ኃይለማርያም…የኮንስትራክሽንና ቤቶች ልማት ቢሮ ኃላፊ

 3.  አቶ ሰሎሞን ኃይሌ……..የመሬት ልማት ቢሮ ኃላፊ

 4.  አቶ ዲላሞ ኦቶሬ……………….የትምህርት ቢሮ ኃላፊ

 5.  አቶ ኃይለ ፍስሃ ………….የከተማ አስተዳደሩ ዋና ስራ አስኪያጅ

 6.  አቶ ጸጋዬ ኃይለማርያም …………….……የፍትህ ቢሮ ኃላፊ

 7.  ወ/ሮ ፍሬሕይወት አያሌው ……………የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ

 8.  አቶ ገብረጻዲቅ ሃጎስ ……………………የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ

 9.  አቶ ጥላሁን ወርቁ …….የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ቢሮ ኃላፊ

 10. ወ/ሮ ብዙነሽ መሰረት ….የሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ

 11. አቶ ኤፍሬም ግዛው ………..የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ

 12. አቶ ሺሰማ ገብረመድህን …..የንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ

 13. አቶ ፎኢኖ ፎላ…የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ኃላፊ

በመሆን በሙሉ ድምጽ በመሾም ቃለ መሃላ ፈጽመዋል፡፡

ተሰናባቹ ከንቲባ ኩማ ደመቅሳና አዲሱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ በማዘጋጃ ቤት ግቢ ውስጥ የመታሰቢያ ችግኝም ተክለዋል፡፡

የ42 አመቱ ጎማሳ አቶ ድሪባ ኩማ የከተማ አስተዳደሩ 30ኛ ከንቲባ ናቸው፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s