ጃዋር፣ቡልቻ፣ሰማያዊ ፓርቲና ተስፋዬ ገ/አብ መቼ ነው መድረክ የሚሆኑን? (ዳዊት ሰለሞን)

daveአለም በምዕራብና ምስራቅ ጎራ ሲከፈል በኢትዮጵያ የተማረ ሊሰኝ የሚችለው ወጣቱ ትውልድ በአፍላ የአብዮቱ ዘመን የአገሪቱን ችግር ለመፍታት በኢትዮጵያ ያለው የብሄር ጭቆና ነው ወይስ የመደብ ጭቆና በማለት ቡድን ለይቶ በእነ ጥላሁን ግዛው፣መለስ ተክሌና ብርሃነ መስቀል ረዳ ፊት አውራሪነት ይጠዛጠዝ እንደነበር የያኔው ትውልድ ምስክር ነው፡፡
የአገሪቱ ችግር የብሄር ጭቆና ነው ያሉ ብረት መዘው ዱር ቤቴ ብለው ሶስት አስርታትን ቆጥረው ምኒልክ ቤተ መንግስት ገቡ፡፡ባስጸደቁት ህገ መንግስት የብሄር ብሄረሰቦች መብት እስከመገንጠል መከበሩን አወጁና የብሄር ጥያቄ ተመልሷል አሉን፡፡በአሩሲ አርባጉጉ አማሮች ተጨፈጨፉ፣ጉራጌዎች ወራሪ ተብለው ተሰደዱ፣ጉራፈርዳ የአማሮችን ስደት አሳየን፣ቤንሻንጉል ተከተለ፡፡
ተስፋዬ ገብረ አብ በኢህአዴግ እቅፍ ውስጥ ሆኖ ‹‹የቡርቃ ዝምታን ጻፈ››ቡርቃ ኦሮሞ በአማራ ስለደረሰበት ጭቆና ቂም ቋጥሮ ዝምታን መምረጡን ነገር ግን ትግሬን ከምድረ ገጽ ለማጥፋት ከአባይ ጋር ማውጋት መጀመሩን ተስፋዬ በእነ በረከት ስምኦን ጀርባ ተከልሎ ነገረን ፡፡
ቡልቻ ደመቅሳ ፓርላማ ውስጥ ባገኙት ወንበር ላይ ቁጢጥ ብለው ‹‹ገለቶማ››እያሉ ኦሮሞው እየተረገጠ ለመሆኑ አቤት አሉ፡፡ከፓርላማ ውጪ ለጋዜጦች በሚሰጧቸው ቃለ ምልልሶች ‹‹አማራ የኦሮሞ ቅኝ ገዢ››ስለ መሆኑ ማስረጃ እያጣቀሱ ተረኩልን፡፡ኦሮሞ ስልጣን አግኝቶ አያውቅም በማለት ሊሞግቱን ሞከሩ፡፡‹‹ምኒልክና አጼ ሃይለስላሴ ኦሮሞ ነበሩ ››ሲባሉ እነርሱ ‹‹ኦርጅናል ኦርሞ አልነበሩም ››አሉን፡፡
ሰማያዊ ፓርቲ አገር አቀፍ ቢሆንም ‹‹አማራ የሚባል ብሄር የለም››አለን፡፡አማራ ኢትዮጵያዊ እንጂ መቼም ቢሆን ‹‹አማራ ነኝ ብሎ አያውቅም ››በማለት ሊቀ መንበሩ ነገሩን፡፡
አሁን ተስፋዬ ገ/አብ የማህበረሰብ ገጾችን ተቆጣጥሯል፡፡በቅርቡ ተስፋዬን በተመለከተ ወጡ የተባሉ ማስረጃዎች ግለሰቡ ኤርትራዊ በመሆኑ ኢትዮጵያን ለመበታተን ሆን ብሎ ከቡርቃ ዝምታ እስከ ጋዜጠኛው ማስታወሻ ያሉትን መጻህፍት ለንባብ ማብቃቱን በመግለጽ በጽሁፎቹ ይዘት ሳይሆን ጽሁፎቹን ለመጻፍ ባነሳሳው ምክንያት ዙሪያ ትኩረት እንድናደርግ እየተወተወትን ነው፡፡
ወጣቱ የፖለቲካ ተንታኝ በማለት እላይ የሰቀልነው ጃዋር መሀመድ ‹‹የሜንጫውን ጉዳይ በማንሳቱንና ከኢትዮጵያዊነቴ በፊት ኦሮሞነቴ ይቀድማል ››ማለቱ አቧራ አስነስቷል፡፡
ዙከርበርግ የፈለሰፈው የማህበረሰብ ድረ ገጽ ከላይ ለመጠቃቀስ በሞከርኳቸው ሰዎች ላይ ዘመቻ በመክፈት የተስፋዬን ሀሳብ በኤርትራዊነት፣የጃዋርን በጭፍን ተቃውሞ፣የሰማያዊን አቋም በዝምታ የቡልቻን በአሮጌ የፖለቲካ ፍልስፍና በመፈረጅ ከጠረጴዛ እንዲወርዱ አድርጓል፡፡
ተስፋዬ እርሾ ሳይኖረው ቀዳዳ ያገኘ አልመሰለውም፣ጃዋር ለራሱ ምክንያታዊ ነው፣ቡልቻ ዘመናቸውን ሁሉ ሲከራከሩበት ኖረዋል፤ሰማያዊ እንደ ፕሮፌሰር መስፍን ያሉ የጉዳዮ አቀንቃኞችን ተከትሏል፡፡ሰዎቹ ወይም ፓርቲው ያነሷቸው ጉዳዮች በራሳቸው የመነሻ ታሪክ አልያም መሬት የረገጠ መነሻ ይኖራቸው ይሆናል፡፡እች እንክፍ በማለትና በማጣጣል ከአዙሪቱ መውጣት አልያም መሸሽ የምንችል አይመስለኝምና፡፡ጠረጴዛ የማዘጋጀት ድፍረት ሊኖረን ይገባናል፡፡
ቡርቃ ከአባይ ለምን ወሬ ጀመረ፣አማራ የሚባል ብሄር የለም፣ከብሄርና ከዜግነት የትኛውን እናስቀድም፣የዚህች አገር ችግር የብሄር ወይስ የመደብ፣ኦሮሞን አማራ የጨቆነው መቼ ነው? ለምን አንወያይባቸውም?

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s