“የሚፈልጉት የእምነት ቃል ነው” ማሰቃየት እና ጎጂ አያያዝ በኢትዮጵያ ማዕከላዊ ፖሊስ ጣቢያ

hrw አንዱ (ፖሊስ) በያዘው ረዥም ጥቁር ዱላ ከኋላ ጭንቅላቴን መታኝ ከዚያ አይኔን በጨርቅ አሰረኝ፤ በመቀጠል ወደ ቢሯቸው ወሰዱኝ፤ ይህንን ያደረጉት መርማሪዎቹ ናቸው…ደጋግመው በጥፊ መቱኝ፡፡ የምነግራቸውን ለመስማት መርማሪዎቹ ዝግጁ አይደሉም፤ በጥቁሩ ዱላ እና በጥፊ ደግመው መቱኝ። እዚያው ክፍል እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ አቆዩኝ፤ በጣም ተዳክሜ ነበር። ከዚያ ወደ ታሰርኩበት ክፍል መለሱኝ እና ሌላ ሰው ወሰዱ፡፡ በሁለተኛው ቀን ምርመራ ድብደባው የባሰ ነበር። የሚፈልጉት ጥፋተኛ ነኝ ብየ እንዳምን ነው 

በ2003ዓ.ም ዓመት አጋማሽ ማዕከላዊ ታስሮ የነበረ ጋዜጠኛ – ናይሮቢ

ሚያዚያ 2004ዓ.ም በኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ መሃል ከአንድ ሆቴል እና አንድ የኦርቶዶክስ ቤቴክርስቲያን አጠገብ በመላ ሃገሪቱ በጣም ታዋቂ የሆነ አንድ ፖሊስ ጣቢያ ይገኛል።ይህም የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ዘርፍ ሲሆን በተለምዶ ማዕከላዊ በመባል ይታወቃል። ተቃዋሚ ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞች፣ የተቃውሞ ሰልፍ አደራጆች፣ በብሄር የተደራጁ አማፅያንን ይደግፋሉ የሚባሉ ሰዎች እና ሌሎችም በርካታ የኢትዮጵያ የፖለቲካ እስረኞች ሲያዙ በቅድሚያ የሚወሰዱት ወደ ማዕከላዊ ነው፡፡ ማዕከላዊ ከገቡ በኋላ ምርመራ ይካሄድባቸዋል። በአብዛኞቹ ላይ ደግሞ ሁሉም ዓይነት እንግልት እና በደል የሚደርስባቸው ሲሆን ይህም ማሰቃየትን ይጨምራል፡፡ በማዕከላዊ የሚገኙት መርማሪ ፖሊሶች ታሳሪዎች ጥፋታቸውን እንዲያምኑ፣ እንዲናገሩ ወይም ሌላ መረጃ እንዲያወጡ የሚያደርጉት በሃይል የማስፈራራት መንገድን በመጠቀም ሲሆን ይህም እስከ ማሰቃየት እና ሌላ ጎጂ አያያዝ እስከ መፈጸም ይደርሳል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ እስረኞች ከጠበቃ እና ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲገናገኙ አይፈቀድላቸውም፡፡ እስረኞቹየመርማሪዎቹን ፍላጎት ለማሟላት በሚያደርጉት ትብብር መጠን በቅጣት ወይም በማበረታቻ መልክ የውሃ፣የምግብ፣ የመብራት እና የሌሎች አስፈላጊ ነገሮች አቅርቦት ሊከለከሉ ወይንም ሊፈቀድላቸው ይችላል፡፡ ይህ ሪፖርት ከ2002 ዓ.ም እስከ 2005 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ በማዕከላዊ የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን፣ ህገወጥ የምርመራ ዘዴዎችን እና የታሳሪዎችን ሁኔታ የሚዳስስ ነው፡

http://www.hrw.org/news/2013/10/18/ethiopia-political-detainees-tortured”>ሙሉ ሪፖርቱን ለማንበብ ይህን ይጫኑ

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s